የአገልግሎት ውል
የመጨረሻ የተሻሻለዉ: ግንቦት 27, 2017
1. መግቢያ
እንኳን ወደ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በደህና መጡ። እነዚህ የአገልግሎት ውሎች ("ውሎች") ስለ አብን ድረ-ገጽ፣ የአባልነት አገልግሎቶችን እና ተዛማጅ ባህሪያትን (በጥቅሉ “አገልግሎቶቹን”) ለመከታተል ይረዳሉ። አገልግሎቶቻችንን ሲያገኙ ወይም ሲጠቀሙ በእነዚህ ውሎች ለመገዛት እንደተስማሙ ይወሰዳል። ማንኛውንም የውሎቹን ክፍል ካልተስማሙ አገልግሎቶቹን ላያገኙ ይችላሉ።
2. የአባልነት መስፈርት
የአብን አባል ለመሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ሊያማሉ ይገባዎታል:
- እድሜዎ 18 አመትና ከዛ በላይ ሊሆን ይገባል
- በምዝገባ ወቅት ትክክለኛ፣ እውነተኛ እና የተሟላ መረጃ ሊያቀርቡ ይገባል
- የአባልነት መረጃዎን ትክክለኛነት ይጠብቁ
- የስነምግባር መተዳደሪያችንን እና እነዚህ ውሎችን ለማክበር መስማማት ይጠበቅቦታል
3. የአባልነት መብቶች እና ግዴታዎች/ኃላፊነቶች
የአብን አባል በመሆንዎ፣ የሚከተሉት መብቶች መተግበር ይችላሉ:
- በፓርቲ ሁነቶች፣ ስብሰባዎች እና ተግባራቶች ውስጥ መሳተፍ ይችላሉ
- ስለ ፓርቲው አዳዲስ መረጃዎች፣ ለውጦች እንዲሁም ዕቅዶች መረጃ ማግኘት ይችላሉ
- በመተዳደሪያ ደንባችን መሰረት በውስጥ የፓርቲ ምርጫ እና የፖሊሲ ውሳኔዎች ላይ ድምጽ መስጠት ይችላሉ
- ለአባላት-ብቻ የተፈቀዱ መርጃዎችን ማግኘት ይችላሉ
የአብን አባል በመሆኖ የሚከተሉት ግዴታዎች/ ሃላፊነት አለቦት:
- ለፓርቲው አባላት እና ለመላው ህዝብ አክብሮት የተሞላበት ምግባርን ሊያሳዩ ይገባል
- የፓርቲውን እሴቶችና መርሆች በአዎንታዊ መልኩ ሊወክሉ/ሊሞግቱ ይገባል
- የአባልነት ክፍያዎችን በወቅቱ መክፈል ይኖርቦታል
- የፓርቲውን ህጎች እና ደንቦች ሊያከብሩ ይገባል
4. አዕምሯዊ ንብረት
የፓርቲያችን ይዘት፣ አደረጃጀት፣ ግራፊክስ፣ ዲዛይን እና ሌሎች ከድረ-ገጻችን ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሚመለከታቸው የቅጂ መብቶች፣ የንግድ ምልክቶች እና ሌሎች የባለቤትነት መብቶች የተጠበቁ ናቸው። ያለ ፓርቲው ፍቃድ ማንኛውንም እንደዚህ ያለ ይዘት ወይም የትኛውንም የአገልግሎታችን ክፍል መቅዳት፣ ማሰራጨት፣ መጠቀም ወይም ማተም የተከለከለ ነው።
5. በተጠቃሚ የመነጨ ይዘት
ማንኛውንም ይዘት ወደ ድረ-ገጻችን ወይም በአገልግሎታችን በኩል በማስገባት/በማስረከብ ዘለቄታዊ፣ የማይሻር እና ሙሉ በሙሉ ፍቃድ ያለው የመጠቀም፣ የማባዛት፣ የመቀየር፣ የማላመድ፣ የማተም፣ የመተርጎም፣ የፈጠራ ስራዎችን የማላቅ፣ የማሰራጨት እና በአለም ዙሪያ በማናቸውም ሚዲያ ላይ የማሳየት መብት ለአብን አሳልፎ መስጠት ይጠበቅቦታል።
6. የስነምግባር መተዳደሪያ ደንብ
የፓርቲው አባላት የስነምግባር ደንቦችን ማክበር ይኖርባቸዋል፤ የሚከተሉትን ክልከላዎች ማክበር ይጠበቅባቸዋል፡-
- በዘር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በዜግነት፣ በአካል ጉዳተኝነት፣ በፆታዊ ዝንባሌ ማንኛውንም አይነት ትንኮሳ ወይም መድልዎ ከማድረግ ሊቆጠቡ ይገባል
- ከአስጊ፣ ተሳዳቢ፣ ክብረ ነክ ወይም ጠበኛ ባህሪ ከማሳየት ሊቆጠቡ ይገባል
- ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃን ከማሰራጨት ሊቆጠቡ ይገባል
- የፓርቲውን ያልተፈቀደ ሚስጥራዊ መረጃ ይፋ ከማድረግ ሊቆጠቡ ይገባል
- ማንኛውንም ህገወጥ ተግባራት ከመፈጸም ወይም ከማስተዋወቅ ሊቆጠቡ ይገባል
7. ከአባልነት መሰናበት
አብን እነዚህን ውሎች፣ የስነ ምግባር ደንቦቹን ወይም በፓርቲ አመራር ተገቢ ነው ተብሎ በሚገመተው ሌላ ምክንያት በመተዳደሪያ ደንባችን ውስጥ የተዘረዘሩትን ሂደቶች በመከተል በማንኛውም ጊዜ አባልነትዎን የማገድ ወይም የማቋረጥ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የዋስትናዎች ማስተባበያ
አገልግሎቶቻችን የሚቀርቡት "እንደነበረ" እና "ባለው" መሰረት ይሆናል። አብን የአገልግሎቶቻችንን አሠራር ወይም በአገልግሎታችን ውስጥ የተካተቱትን መረጃዎች፣ ይዘቶች፣ ቁሳቁሶች ወይም ምርቶች በተመለከተ ምንም አይነት ውክልና ወይም ዋስትና አይሰጥም።
9. የተጠያቂነት ገደብ
አገልግሎታችንን ከመጠቀም ጋር ተያይዞ በቀጥታ፣ በተዘዋዋሪ ወይም በአጋጣሚ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ጉዳት አብን ተጠያቂ አይሆንም።
10. ውሎች ላይ የሚኖሩ ወይም ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦች
አብን እነዚህን ውሎች በማንኛውም ጊዜ የመቀየር መብቱ የተጠበቀ ነው። ጉልህ ለውጦች በሚኖሩ ወቅት በድረ-ገፃችን ወይም በኢሜል ለተመዘገቡ አባላቶቻችን እናሳውቃለን። ለውጦችን ይፋ ካደረግን በኋላ አገልግሎቶቻችንን ከተጠቀሙ ያደረግናቸውን ለውጦች እንደተቀበሉ ይወሰዳል።
11. ገዢ ህግ
እነዚህ ውሎች የሚተዳደሩት እና መተርጎም ያለባቸው የህግ ድንጋጌዎች ግጭትን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ አብን በተመዘገበበት የዳኝነት ህግ መሰረት ነው።
12. እኛን ማግኘት ከፈለጉ
በውሎቹ ዙሪያ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎች ካሎት፣ እባክዎን በሚከተለው አድራሻ ያግኙን፡-
አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ
አምባሳደር ሲኒማ ከሃራምቤ ሆቴል አጠገብ
አራዳ ክፍለ ከተማ ,አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
+251 111 550 999
ኢሜል ይላኩልን
አጠቃላይ ጥያቄዎች፡
info@nama.gov.et