የግለሰብ መብትን ያለመጣስ/ማክበር መተዳደሪያ ደንብ
የመጨረሻ የተሻሻለዉ: ግንቦት 27, 2017
1. መግቢያ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ("ዓብን" "እኛ"ወይም "የእኛ" የእርስዎን የግል ፍላጎት ያከብራል። አብን የእርስዎን የግል መረጃ ለመጠበቅ ምንግዜም ቁርጠኛ ሆኖ ይሰራል። ይህ የግለሰብ መብትን የሚያከብር መተዳደሪያ ፖሊሲ ፓርቲያችንን በአባልነት ሲቀላቀሉ ወይም ድረ-ገጻችንን ሲጠቀሙ መረጃዎን እንዴት እንደምንሰበስብ፣ እንደምንጠቀም ብሎም እንደምንጠብቅ ያብራራል።
2. የምንሰበስባቸው መረጃዎች
የሚከተሉትን የመረጃ ዓይነቶች ልንሰበስብ እንችላለን፡-
2.1 የግለሰብ መረጃ
- ግለሰቡን የማግኛ ዘዴዎች (ስም ፣ ኢሜል ፣ ስልክ ቁጥር ፣ የፖስታ አድራሻ)
- ግለሰባዊ መገለጫ (የትውልድ ቀን, ጾታ, ሥራ)
- የቤተሰብ መረጃ (የጋብቻ ሁኔታ፣ የደባል ነዋሪዎች ብዛት፣ የወላጅ ስሞች)
- ዳራዊ መረጃ (የትውልድ ቦታ ፣ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ፣ ሃይማኖት ፣ የትምህርት ደረጃ)
- የአደጋ ጊዜ ተጠሪ አድራሻ
- የአባልነት ሁኔታ እና የሁዋልዮሽ ታሪክ
- የአባልነት የክፍያ መረጃ (የሚመለከቶ ከሆነ)
2.2 የፖሊሲው አጠቃቀም መረጃ
- ከድረ-ገፃችን እና ከአገልግሎቶቻችን ጋር ስላሎት ግንኙነት መረጃ
- የአይፒ አድራሻ ፣ የኢንተርኔት መጠቀሚያ አይነት ፣ የኢንተርኔት መጠቀሚያ መሣሪያ
- የተጎበኙ ገጾች እና ጥቅም ላይ የዋሉ መገለጫዎች
- የማመሳከሪያ/የማጣቀሻ ምንጮች እና መውጫ ገጾች
3. ፓርቲያችን የግለሰብ መረጃን እንዴት ይሰበስባል
መረጃን የምንሰበስብባቸው መንገዶች፡-
- የአባልነት ማመልከቻዎች እና ቅጾችs
- ከፓርቲያችን ጋር የሚደረግ ተግባቦት
- የኩነት ምዝገባዎች እና ኩነት ላይ መገኘት
- የዳሰሳ ጥናቶች እና የግብረመልስ ቅጾች
- በፓርቲያችን ድረ-ገጽ ላይ የሚታዩ ኩኪዎች እና ቴክኖሎጂዎች
- የሶስተኛ ወገን ምንጮች፣ ለምሳሌ ይፋዊ/ህዝባዊ ዳታቤዞች ወይም የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች (ፍቃድዎን ያማከለ)
4. መረጃዎን እንዴት እንጠቀማለን
የሚሰጡንን መረጃ ለሚከተሉት ዓላማዎች እንጠቀማለን፡:
- አባልነትዎን ለማሳለጥ ብሎም ለማስተዳደር
- ፓርቲያችን ስለሚያደርገው ዝግጅቶች እንዲሁም ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ወይም ኩነቶች ከእርስዎ ጋር ለመወያየት
- የአባላቶቻችንን ከባቢያዊ ስብጥር ለመረዳት
- የምንሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሻሻል እንዲሁም አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመቅረጽ
- ጥናትና ምርምር ለመከወን እንዲሁም የምርምሩ ውጤት ላይ አስፈላጊ ትንተና ለማካሄድ
- ህጋዊ ግዴታዎቻችንን ለመወጣት
- የፓርቲያችንን ስርዓት፣ ደህንነት እና ተአማኒነት ለመጠበቅ
5. መረጃን ለማጋራትና ለተገቢው አካል ይፋ ለማድረግ
የእርስዎን የግለሰብ መረጃ ለሚመለከታቸው አካላት ልናጋራ እንችላለን፡-
- የፓርቲ ኃላፊዎች እና ፍቃድ የተሰጣቸው በጎ ፈቃደኞች ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ሲፈልጉ
- የፓርቲያችን አገልግሎት አቅራቢዎች (ለምሳሌ፣ የክፍያ እና የኢሜይል አገልግሎት አቅራቢዎች)
- የህግ እና የቁጥጥር ባለስልጣናት (የህግ አግባብ ሲኖራቸው)
- ሚስጥራዊ ውህደት፣ ሽያጭ ወይም ሌላ የንብረት ዝውውር ሲኖር
ያለፍቃድዎ የግል መረጃዎን ለገበያ አላማ አናውልም።
6. የመረጃ ደህንነት
የእርስዎን ግላዊ መረጃ ከአደጋ ለመጠበቅ ተገቢውን ቴክኒካዊ እና ተቁዋማዊ እርምጃዎችን እንተገብራለን። ነገር ግን የእርስዎን መረጃ ለመጠበቅ ጥረት ስናደርግ ምንም አይነት የበይነመረብ ወይም የኤሌክትሮኒክስ ማከማቻ ደህንነቱ መቶ በመቶ የተጠበቀ አለመሆኑን ከወዲሁ ሊረዱን ይገባል።
7. መብቶችዎ እና ምርጫዎችዎ
የግል መረጃዎን በተመለከተ እንደሚገኙበት አካባቢ የሚከተሉት መብቶች ይኖርዎታል ፡-
- የእራስዎን የግል መረጃ መመልከት ይችላሉ
- ስህተት የሆነ ወይም ያልተሟላ መረጃዎን ማስተካከል ይችላሉ
- የሰጡት መረጃዎ እንዲሰረዝ መጠየቅ ይችላሉ
- ተገቢ አይደሉም ብለው ያሰቡትን የፓርቲው ተግባራትን መቃወም ወይም ማስቆም ይችላሉ
- የመረጃ ፍሰት (መረጃዎን በተዋቀረ እና በማሽን ሊነበብ በሚችል መልኩ ማግኘት ይችላሉ)
- ፍቃድዎን ሂደትን መሰረት ባደረገ መልኩ ማንሳት ይችላሉ
ከላይ የተዘረዘሩ መብቶችዎን ለመጠቀም፣ በዚህ መመሪያ መጨረሻ ላይ የቀረበውን መረጃ በመጠቀም እባክዎ ያግኙን።
8. ኩኪዎች እና መሰል ቴክኖሎጂዎች
ድረ-ገፃችን የእርስዎን ተሞክሮ ለማላቅ፣ የአጠቃቀም ሂደትዎን ለመተንተን እና ግላዊ ዕሳቤዎን ለማቅረብ ኩኪዎችን እና መሰል ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማል። ይህ በድረ-ገፃችን ላይ የተወሰኑ ተግባራትን ሊገድብ ቢችልም ኩኪዎችን መቆጣጠር ይችላሉ።
9. የህጻናት/የታዳጊዎች ግላዊ ፍላጎት/መብት/መረጃ
አገልግሎታችን ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ግለሰቦች አያገለግልም። የህጻናትን የግል መረጃ ሆን ብለን አንሰበስብም። በስህተት መረጃ እንደሰበሰብን ካመኑ፣ እባክዎን ወዲያውኑ ያሳውቁን።
10. መረጃን ይዞ ማቆየት
ረዘም ያለ የማቆያ ጊዜ ካልተፈለገ ወይም በሕግ ካልተፈቀደ በቀር በዚህ የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ለመፈጸም አስፈላጊ እስከሆነ ድረስ የእርስዎን የግል መረጃ እንይዘዋለን። የማቆያ ጊዜዎችን በምንለይበት ጊዜ የመረጃውን መጠን፣ ተፈጥሮ እና አንገብጋቢነት፣ ያልተፈቀደ አጠቃቀም ወይም ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት እና የሚመለከታቸው የህግ መስፈርቶችን እንመለከታለን።
11.በመመሪያው ላይ የተደረጉ ለውጦች
በአሰራሮቻችን ወይም በህጋዊ መስፈርቶች ላይ ለውጦችን ለማንፀባረቅ ይህ መመሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊሻሻል ይችላል። የተሻሻለውን ፖሊሲ በድረ-ገፃችን ላይ በመለጠፍ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኢሜይል እናሳውቅዎታለን።
12. እኛን ማግኛ መንገድ
ይህን መመሪያ በሚመለከት ስጋቶች ወይም ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎን በሚከተለው አድራሻችን ያግኙን፡
አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ
አምባሳደር ሲኒማ ከሃራምቤ ሆቴል አጠገብ
አራዳ ክፍለ ከተማ ,አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
+251 111 550 999
ኢሜል ይላኩልን
አጠቃላይ ጥያቄዎች፡
info@nama.gov.et